ስለ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአማርኛ ተናጋሪ ቤተ ክርስቲያን አባላት ጋር ለመማር፣ ለማምለክ እና ለማክበር የጸጋ የመጽሐፍ ቅዱስ ኅብረት ቤተክርስቲያንን ይቀላቀሉ።
እግዚአብሔርን በማምለክ፣ በመጸለይ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ግንዛቤ በምናሳድግበት አንድ ላይ በምንሰባሰብበት ትርጉም ያለው ፕሮግራም ላይ ይቀላቀሉን።
በአካል በመገናኘት በምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ይቀላቀሉን። በዚህ ጊዜ ኢየሱስን የምናከብርበት፣ እራሳችንን የምናንጽበት እና መንፈሳዊ ማንነታችንን የምናዳብርበት በአካል ለምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና ጸሎታችን ይቀላቀሉን።
ኦንላይን በመገናኘት በምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ይቀላቀሉን። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍለ ጊዜዎች ከቤትዎ ሆነው መንፈሳዊ ጉዞ ይጀምሩ። በስልክ ቁጥር 416-839-7968 ወይም 647-608-8189 ዕሮብ 7፡30 PM
የቤተ ክርስቲያናችንን አባሎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ደቀመዛሙርት ማድረግና ጥሪያቸውን በሚገባ አውቀው አምላካቸውን እንዲያገለግሉ ማስታጠቅ እና በጸሎት፣ በአምልኮ እና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዲታዘዙ የአባሎቻችንን እምነት እናሳድጋለን።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለክርስቲያኖች በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አማኞች እምነታቸውን እንዲያድግ ፤ ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን ዝምድና እንዲጠነክርና የጽድቅን ሕይወት እንዲመሩ እናስጠናቸዋለን።
በየሳምንቱ በእምነት እና በአንድነት መንፈስ በአምላካችን እግር ሥር ልባችንን ለማፍሰስ እንሰበሰባለን። በዚህ ጊዜ ስለ ልጆችና ወጣቶች ፤ ስለ ሀገር ፤ ስለ ትሁት ልብ ፤ ስለ ጽኑ እምነት ፤ ስለ ፈውስ ፤ ስለ ሰላም ፤ ስለ ፍቅር ፤ ስለ ደስታ ፤ እና ስለ መንፈስ ፍሬዎች . . ወዘተ እንፀልያለን።
ጎልማሶችን በፍቅር እና በጥበብ በመምራት በኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት ወደተሞላ ሕይወትና ልባቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ እንዲያደርጉ በመንከባከብ መንገዱን እንዲያውቁ እናግዛቸዋለን።
ልጆችን በፍቅር እና በጥንቃቄ በመምራት የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት እናስተዋውቃቸዋለን። ከእድሜ ጋር በሚስማማ ትምህርት እና ጸሎት እምነታቸውን ለማሳደግ እንጥራለን።
አንድ አማኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት በውሃ ውስጥ በመጥለቅ፣ በኃጢአት ንስሐ እና እርሱን ለመከተል ቃል መግባታቸውን የሚያሳዩበት ትርጉም ያለው መንፈሳዊ ሥርዓት በመሆኑ ከመሠረታዊ የክርስትና ትምህርት በመቀጠል እናጠምቃለን።
ትርጉም ላለው ህብረት፣ መንፈሳዊ እድገት እና በእምነት ጉዞዎ ውስጥ ድጋፍ ለማግኘት የቅርብ የተሳሰረ የጥናት ቡድኖቻችንን ይቀላቀሉ።
ይህ ተሞክሮ የተቻለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባመጣው ድህንነ ነው።